ማስተር ፕላንና የተማሪዎች ተቃዉሞ በኦሮሚያ ክልል DW

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሚገኙ ከአንደኛ እስከ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን እና የመልካም አስተዳደር ጉድለትን በመቃወም ላይ ናቸው። በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙት ተማሪዎች ተቃዉሟቸዉን ካለፉት ሁለት ሳምንት ጀምሮ እያካሄዱ መሆኑ ታዉቋል።

ከኅዳር 9 ቀን 2008 ዓ,ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጃ የጋራ ማስተር ፕላን እና የመልካም አስተዳደር ጉድለትን በመጠቆም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተማሪዎች ተቃዉሞ እያደረጉ ነዉ። ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸዉ በሰላም በሚካሄድ ትግል ዉስጥ ችግርን በይፋ መግለጽ በሕገ መንግስቱ የተደነገገ መብት መሆኑን እንደሚያምኑ የሚናገሩት ተማሪዎች የተጠቀሰዉ የማስተር ፕላን ልዩ ዞኑ ዉስጥ የሚገኙ ኗሪዎችን ከመሬታቸዉ እንደሚያፈናቅል ያም አግባብ እንዳልሆነ ይናገራሉ። ከዚህም ሌላ ከአደስ አበባ ከተማ የሚወጡ ፈሳሾች ለሰዉም ሆነ ለእንስሳዎች ጠንቅ በመሆኑ መፍትሄ እንዲፈለግ ተቃዉሞ ማሰማታቸዉን ያስረዳሉ። በተጨማሪም የመልካም አስተዳደር እጥረት ያመጣዉ ነዉ ያሉት በግንጭ የሚገኘዉን የጭልሞ ጫካ ለግለሰቦች መንግስት ሸጧል በሚልም ተማሪዎቹ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ተቃዉሟቸዉን አሰምተዋል።
በተቃዉሞዉ ወቅትም ቁጥራቸዉ ብዙ የሆኑት ተማሪዎች እንደታሰሩ፣ በፖሊስ ሃይልም ድብደባም የተጎዱ መኖራቸዉን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁ እማኝ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። <<በአምቦ የመሰናዶ ትምህርት ቤት እና በድሬ እንጭኒ ተማሪዎች ለሰለማዊ ሰልፍ ወጥተዉ ነበር። እሱንም ተከትሎ የኦሮሚያ ፖሊስ ተማሪዎቹን ማሰር ጀመረ። ሕዳር 14 ዘጠኝ ተማሪዎች ታስረዋል፣ ትላንትም ብዛታቸዉን ባላዉቀዉም ወደ አምስት ተማርዎች መታሠራቸዉን ሰምቼ ነበር። በተጨማሪ እሄን እስር አምልጠዉ ወደ ፊንፊኔ የሸሹ ተማሪዎች እንዳሉ ሰምቼ ነበር።>>

 Dr. Merera Gudina Addis Abeba Äthiopien Oromo Pressekonferenz PK

ስምንት ከተሞችን ያቀፈዉ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በዚህ የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን እንዲገባ ሲታቀድ የፌድራል መንግስትም ሆነ የኦሮሚያ ምክር ቤት ህዝብን ጠርቶ አለመወያየቱ ከዛም አልፎ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች መድረኩን አለመፍቀዱ ችግሩ እንዲባባስ አድርጓል በሚል የሚተቹ አሉ። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ በቀለ ናጋ ለዶቼ ቬሌ ይህን አስመልክተዉ ሲናገሩ፤ <<የመሬት ጉዳይ የመኖር ህልዉና ጉዳይ ነዉ። እናም የኦሮሞ ህዝብ እየተቸገረ ስለሆነ ይህ የመሬት ዘረፋ በአሰቸኳይ እንዲቆም እንፈልጋለን። ባለፈዉ የጨፌ ኦሮሚያ ያወጣዉ ሕግ፣ ከተሞች መቀላቀልና አንድ ማድረግ ይችላሉ የሚለዉ፣ ባህሉንና ቋንቋዉን የሚያጠፋ ሆኖ ስለታየን፣ በጽሑፍም ጠይቀናል። እናም ሰዉ በሰላማዊ መንገድ እየታገለ ስለሆነ ይህ አዋጅ መቆም አለበት እንላለን። ሁለተኛ ኦሮሞ ለልማቱ ተብሎ ከመሬቱ የሚነሳ ከሆነ ያ ልማት እሱን መጥቀም አለበት። ያም ማለት፣ መሬቱን ይዞ ካለዉ አካል ጋር እንደግለሰብ አክስዮን ኖሮት የሚቋቋመዉ ኢንዱስትሪ ዉስጥ ሚና ሊኖረዉ ይገባል ነዉ የምንለዉ። ጎረቤቶቻችንም ይህን ችግር ከእኛ ጋር እየተካፈሉ መከላከል አለባቸዉ።>>
ሌላዉ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ የ89 አመት አዛዉንት በበኩላቸዉ ሱሉልታ አካባቢ ባለፈዉ ሳምንት ጀምሮ 600 ቤተሰብ ይኖርበት በነበረ ቦታ ላይ መንግስት ኢንዱትሪ ለመገንባት በመፈለጉ ካሳ ሳይሰጥ ኗሪዎቹን እንዳስነሳ ይናገራሉ። ለዚህም ወደ ኦሮሚያ ክልል መንግስት ድረስ ሄደዉ ቢጠይቁም መልስ አለማግኘታቸዉን እንደዉም እዚያ የሚገኙ የመንግስት ካቢኔዎች በእስር እንዳሰፈሯሯቸዉ ይናገራሉ። አዛዉንቱ አክለዉም፤ <<የተወለድንበትን ቦታ ትተን የት ነዉ የምንሄደዉ? ልጆች አሉን፣ እንስሶዎች አሉን፣ የት ነዉ የምንሄደዉ? አዉሬ ይበላናል፤ ማንስ ያስጠጋናል።>>

ይህን በሚመለከት ምላሽ ለማግኘት ከፌዴራልም ሆነ ከኦሮሚያ መንግስት የሚመለከታቸዉን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሰ

 

http://www.dw.com/am/%E1%88%9B%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%88%AD-%E1%8D%95%E1%88%8B%E1%8A%95%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%88%9B%E1%88%AA%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%89%B0%E1%89%83%E1%8B%89%E1%88%9E-%E1%89%A0%E1%8A%A6%E1%88%AE%E1%88%9A%E1%8B%AB-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D/a-18889605?maca=am-Twitter-sharing

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s