“በስልክ የማውራት አሸባሪነት” (Speaking on phone labeled “terrorism”)

በሽብር የተከሰሱ ሰዎች ላይ በተደጋጋሚ እና በተለይ ከሚቀርቡ የማስረጃ ዓይነቶች አንዱ የስልክ ግንኙነት ነው፡፡ ከላይ በጠቀስነው መዝገብ ውስጥ ብቻ ክስ ሆነው የቀረቡትን የስልክ ግንኙነቶች እንመልከት፡-

  • 1ኛ ተከሳሽ ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ‹‹በ 2000 ተድላ ደስታ ከተባለ የሽብር ድርጅቱ አባልና አመራር ጋር በስልክ እና በፌስቡክ›› በማውራት
  • 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ አያሌው ‹‹ዘመኑ ካሴ ከተባለ የግንቦት ሰባት ታጣቂ›› ጋር በጥር 14/2005 በስልክ በማውራት፤
  •  3ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ሺበሺ ‹‹የግንቦት ሰባት አመራር ከሆነው ፋሲል የኔ አለም ›› ጋር በየካቲት 29/2003 በስልክ በማውራት፤
  •  4ኛ ተከሳሽ አብርሃ ደስታ ‹‹የደ.ም.ሕ.ት. አመራር ከሆነው ጎይቶም በርሄ ›› ጋር ጥር 3/2006 በስልክ በማውራት፤
  •  5ኛ ተከሳሽ የሺዋስ አሰፋ ‹‹የግንቦት ሰባት አመራር ከሆነው ፋሲል የኔአለም›› ጋር ጥቅምት 14/2006 በስልክ በማውራት፤
  • 10ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ተፈሪ፣ የግንቦት ሰባት ክንፍ ከሆነው የአ.ዴ.ኃ.ን አባል ጋር ሕዳር 2003 በስልክ በማውራት፤

4Z9Article

እነዚህ የስልክ ግንኙነቶች ያለሌላ ተጨማሪ ማስረጃ በብቸኝነት የክስ መመስረቻ መሆናቸው ደግሞ ክሱን ተአማኒነት ያሳጡታል፡፡ ዜጎች የስልክ ግኑኝነቶችን በሙሉ እንዲፈሩም ያደርጋቸዋል፡፡ በሽብርተኝነት በተጠረጠሩ ድርጅቶች ውስጥ በዐቃቤ ሕጉ ቃል ብቻ አባል ናቸው የተባሉ ሰዎች ስለደወሉለት ብቻ የተደወለለት ሰው ‹‹አሸባሪ›› ተብሎ ይከሰሳል፡፡ ፈቅዶ ባልተደወለለት ስልክ ወንጀለኛ ነህ የሚባልበት አሰራር ከኢትዮጵያ ውጪ ያለ አይመስልም፡፡ አንዳንዶቹ የስልክ ጥሪዎች የተደረጉት ‹‹ሽብርተኛ ናቸው›› በተባሉ ድርጅቶች ውስጥ ባሉ እና በሚታወቁ ግለሰቦች ሳይሆን የአቃቤ ህግ ቃል ብቻ ያልሆነውን ነው ብሎ ስላቀረበ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የተፈረደባቸው ብዙ ናቸው፡፡ ሳይፈረድባቸው ራሳቸውን ለመከላከል ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ የተደረጉትም የዚያኑ ያክል ናቸው፡፡ በ2000 የፀረ ሽብርተኝነቱ አዋጅ አልወጣም ነበር፤ ሽብርተኛ የተባሉ ድርጅቶችም አልነበሩም፡፡ ክሱ ላይ ግን በዚያ ወቅት የተደረገ የስልክ ግንኙነት ተጠቅሷል፡፡

በሁሉም የሽብር ክሶች ውስጥ copy/paste የተደረገች ውንጀላ አለች፤ ‹‹ራሱን [እከሌ ]ብሎ ከሚጠራው አሸባሪ ቡድን ግንኙነት በመፍጠርና ተልእኮ በመቀበል ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ በማሰብ . . . ‹‹የምትል ነች፡፡ ይህች ቃል ዐቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎች ላይ ምንም ዓይነት ድርጊት ሳይጠቅስ የሚያስቀጣበት ውንጀላ  ነች፡፡ በዚሁ በነዘላለም መዝገብም ላይ በተደጋጋሚ ተጠቅሳለች፡፡ በስልክ አንድ ሰው ጋር ያወራሉ ከዚያ ተልእኮ ይቀበላሉ፡፡ ሽብር ማለት በቃ ይኽው ነው፡፡

http://zone9ethio.blogspot.be/2015/03/blog-post.html

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s